ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራው በግም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚቀርበው የእህል ቍርባን ደግሞ ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።
ለአንዱ ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአንድ አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን አድርጎ፣ ለእያንዳንዱም ኢፍ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ዐብሮ ያቅርብ።
በበዓላትና በተወሰኑት በዓላት፣ ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራ በጉም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ግን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።
ከአውራ በጉ ጋራ የሚቀርበው የእህል ቍርባን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚቀርበውም የእህል ቍርባን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።
“ሰውየው ድኻ ከሆነና እነዚህን ለማቅረብ ዐቅሙ ካልፈቀደለት፣ ማስተስረያ እንዲሆነው የሚወዘወዝ አንድ ተባዕት የበግ ጠቦት ለበደል መሥዋዕት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ደግሞም አንድ ሎግ ዘይት ያምጣ፤
“ ‘በየወሩ መባቻ እንከን የሌለባቸውን ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ ዓመት የሆናቸውን ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።
አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን እያንዳንዱ ይስጥ።