ይህም መሬት በእስራኤል ምድር የገዢው ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ ገዥዎቼ ሕዝቤን አይጨቍኑም፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት በየነገዳቸው ርስት እንዲይዙ ይፈቅዱላቸዋል።
ጨካኝ ገዥ ማመዛዘን ይጐድለዋል፤ አለአግባብ የሚገኝን ጥቅም የሚጸየፍ ግን ዕድሜው ይረዝማል።
“የአንተ ዐይንና ልብ ያረፉት ግን፣ አጭበርብሮ ጥቅምን በማግኘት፣ የንጹሑን ደም በማፍሰስ፣ ጭቈናንና ግፍን በመሥራት ላይ ብቻ ነው።”
“እነሆ፤ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣ በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል” ይላል እግዚአብሔር።
ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤ እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ። ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ።
ምሽጎቻቸውን አወደመ፤ ከተሞቻቸውንም ባድማ አደረገ፤ ምድሪቷና በውስጧ ያሉት ሁሉ፣ ከግሣቱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።
በውስጧ የሚገኙ መኳንንቷ ግዳይ እንደሚቦጫጭቁ ተኵላዎች ናቸው፤ በግፍ ትርፍ ለመሰብሰብ ደም ያፈስሳሉ፤ ሕይወትም ያጠፋሉ።
“ ‘እነሆ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል መስፍን ደም ለማፍሰስ ሥልጣኑን ይጠቀማል።
ገዥው ከንብረታቸው በማፈናቀል፤ የትኛውንም የሕዝቡን ርስት መውሰድ አይገባውም፤ ለወንድ ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ንብረት ነው፤ ይኸውም ከሕዝቤ ማንም ከርስቱ እንዳይነቀል ነው።’ ”
የእስራኤል ቅሬታዎች ኀጢአት አይሠሩም፤ ሐሰትም አይናገሩም፤ በአንደበታቸውም ተንኰል አይገኝም። ይበላሉ፤ ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።”
እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን?
ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
እስራኤላውያን ድርሻ ድርሻቸውን ከያዙ በኋላ፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት፤