Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 45:3

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተቀደሰውም ስፍራ ላይ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱም ዐሥር ሺሕ ክንድ ለካ፤ በዚህም ውስጥ መቅደሱ፣ ይኸውም ቅድስተ ቅዱሳኑ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤

ከዚሁም ዐምስት መቶ ክንድ በዐምስት መቶ ክንድ፣ ዙሪያው ዐምሳ ክንድ ባዶ ቦታ ቀርቶ፣ ለመቅደሱ ይሁን።

ይህም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉና፣ በእግዚአብሔር ፊት ለአገልግሎት ለሚቀርቡ ካህናት፣ ቅዱስ የሆነ የምድሪቱ ክፍል ይሆናል።

ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል።

“ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች