ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ ባዕድ በእስራኤላውያን መካከል የሚኖር ቢሆንም እንኳ ወደ መቅደሴ አይግባ።
ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?
ምስክርነትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል።
“በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፣ በቤተ ሰቡ ያሉት ወንዶች ሁሉ መገረዝ አለባቸው፤ ከዚያም እንደ ተወላጅ ተቈጥሮ የሥርዐቱ ተካፋይ ይሁን። ያልተገረዘ ወንድ ግን የፋሲካን ምግብ አይብላ።
ከአስጸያፊ ሥራችሁም ሌላ ምግብ፣ ሥብና ደም ስታቀርቡ ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን እንግዶች ወደ መቅደሴ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አረከሳችሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አፈረሳችሁ።
“ከዚያም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር፣ በቅዱሱ ተራራዬ በጽዮን እንደምኖር ታውቃላችሁ፤ ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲያ ባዕዳን አይወርሯትም።
ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣
በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ ምንቸቶቹን በመውሰድ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያ ቀን በእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ከነዓናዊ አይገኝም።
ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጕዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖር ልጅ በለዓምን አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።
በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፣ ርኩሰትን የሚያደርግና ውሸትን የሚናገር ሁሉ አይገባባትም።