የመሠዊያው ምድጃ እኩል በእኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ዐሥራ ሁለት ክንድ፣ ወርዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነው።
ከዚያች እንደ ብረት ማቅለጫ እቶን እሳት ከሆነችው፣ ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህም ርስትህም ናቸውና።
ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ።
በዙሪያቸው ካሉት አሕዛብ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም፣ መሠዊያውን በቀድሞው መሠረት ላይ ሠሩ፤ በመሠዊያውም ላይ ጧትና ማታ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
“ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ ዐምስት፣ ወርዱም ዐምስት ክንድ ሆኖ ባለአራት ማእዘን ይሁን።
ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣ አርኤል፣ አርኤል ወዮልሽ! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።