ከዚያም ወደ ውስጥ ገባ፤ የመግቢያውን ዐምዶች ለካ፤ የእያንዳንዱም ወርድ ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ሲሆን፣ ግራና ቀኝ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር።
ክፍሎቹ እንደ መተላለፊያ በረንዳዎቹ ከግራና ከቀኝ በኩል ትንንሽ መስኮቶች አሏቸው። በዙሪያው ያሉ መስኮቶች በመግቢያው በር ፊት ለፊት የነበሩ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ክፍል ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾበታል።
ወደ ቤተ መቅደሱም መተላለፊያ በረንዳ አመጣኝ፤ የመተላለፊያ በረንዳዎቹን ዐምዶች ለካ፤ በአንዱ በኩል ዐምስት ክንድ በሌላውም እንዲሁ ዐምስት ክንድ ነበር። የመግቢያው በር ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ ሲሆን፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ስፋት በአንዱ በኩል ሦስት ክንድ፣ በሌላውም እንዲሁ ሦስት ክንድ ነበሩ።
ከዚያም ወደ መቅደሱ አገባኝ፤ ዐምዶቹንም ለካ፤ የዐምዶቹም ወርድ በአንዱ በኩል ስድስት ክንድ፣ በሌላውም በኩል ስድስት ክንድ ነበር።