Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 41:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሰው ፊት ያለው ኪሩብ በአንድ በኩል ወዳለው ዘንባባ የዞረ ሲሆን፣ የአንበሳ ፊት ያለውም በሌላ በኩል ወዳለው ዘንባባ ዞሮ ነበር። ሁሉም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ላይ ተቀርጸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳርና ዳር ባሉት ድጋፎች መካከል በሚገኙት ጠፍጣፋ ናሶች ላይ የአንበሶችን፣ የኰርማዎችንና የኪሩቤልን ምስል አደረገ፤ በድጋፎቹም ላይ እንደዚሁ አደረገ። ከአንበሶቹና ከኰርማዎቹ በላይና በታች በኩል ደግሞ የአበባ ጕንጕን የሚመስሉ ተቀጥቅጠው የተሠሩ ቅርጾች ነበሩ።

ፊታቸውም እንዲህ ነበር፤ አራቱም እያንዳንዳቸው የሰው ፊት ነበራቸው፤ በቀኝ በኩል የአንበሳ ፊት፣ በግራ በኩልም የበሬ ፊት ነበራቸው፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የንስር ፊት ነበራቸው።

እያንዳንዱም ኪሩብ አራት አራት ፊት ነበሩት፤ ይኸውም አንደኛው ፊት የኪሩብ፣ ሁለተኛው የሰው ፊት፣ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፣ አራተኛውም የንስር ፊት ነበር።

እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊት፣ አራት አራት ክንፍ፣ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰውን እጅ የሚመስል ነበራቸው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች