Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 41:15

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ከቤተ መቅደሱ በስተጀርባ ከግቢው ትይዩ ያለውን ሕንጻ ለካ፤ ይህም በግራና በቀኝ ያሉትን መተላለፊያዎች የሚጨምር ሲሆን፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር። የውጩ መቅደስና የውስጡ መቅደስ ከአደባባዩ ትይዩ ያለው መተላለፊያ በረንዳ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቤታችን ተሸካሚዎች ዝግባዎች፣ የጣራችን ማዋቀሪያዎችም ጥዶች ናቸው።

የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ ጠጕርሽ የሐር ጕንጕን የመሰለ ነው፤ ንጉሡም በሹሩባሽ ታስሮ ተይዟል።

በምዕራብ በኩል ከቤተ መቅደሱ ግቢ ትይዩ የሆነው ሕንጻ ወርድ ሰባ ክንድ ነበር። የሕንጻው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዘጠና ክንድ ነበር።

ከዚያም ቤተ መቅደሱን ለካ፤ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ የቤተ መቅደሱ ግቢና ሕንጻ ከነግንቡ ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ሆነ።

በምሥራቅ በኩል የቤተ መቅደሱ ግቢ ስፋት፣ ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን ስፍራ ጨምሮ አንድ መቶ ክንድ ነበር።

እንዲሁም መድረኮቹና ጠበብ ያሉት መስኮቶች፣ በሦስቱም ዙሪያ ያሉት መተላለፊያዎች፣ ከመድረኩ በላይና ራሱ መድረኩም ጭምር ሁሉም በዕንጨት ተለብዶ ነበር። ወለሉ፣ እስከ መስኮቶቹ ያለው ግንብና መስኮቶቹ ተለብደዋል።

ከውስጡ መቅደስ መግቢያ በላይ ያለው ውስጡና ውጩ እንዲሁም በውስጡ መቅደስና በውጩ መቅደስ መካከል ያለው ሁሉ ዙሪያውን

ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ።

በደቡብ በኩል የውጩን አደባባይ ግንብ ተከትሎ፣ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ጋራ የተያያዙና ከውጩ ግንብ ጋራ ትይዩ የሆኑ ክፍሎች አሉ፤

በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤

ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ።

የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና።

“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች