ለሚቃጠለው መሥዋዕት መገልገያ የሆኑ፣ ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ የእያንዳንዳቸው ርዝመት፣ ወርድና ቁመት አንድ ክንድ ተኩል ነበር፤ በእነዚህም ላይ ለሚቃጠለው መሥዋዕትና ለሌላውም መሥዋዕት ማረጃ የሚሆኑ መሣሪያዎች ይቀመጡባቸው ነበር።
ከድንጋይ መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ ከጥርብ ድንጋይ አትሥራ፤ መሣሪያ የነካው ከሆነ ታረክሰዋለህና።
በመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳው ሥር በግራና በቀኝ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት የሚታረዱበት ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች አሉ።
እንዲሁም አንዳንድ ስንዝር የሚሆኑ ሁለት ጣት ያላቸው ሜንጦዎች በግንቡ ዙሪያ ተንጠልጥለው ነበር፤ ጠረጴዛዎቹም የመሥዋዕቱ ሥጋ ማስቀመጫ ነበሩ።