ከመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳ በስተ ውጭው ግንብ ወደ ሰሜን በር መግቢያ ላይ ባሉት ደረጃዎች አጠገብ ከግራና ከቀኝ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ይገኛሉ።
በመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳው ሥር በግራና በቀኝ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የኀጢአትና የበደል መሥዋዕት የሚታረዱበት ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች አሉ።
ስለዚህ በአንዱ በር በኩል አራት፣ በሌላውም በኩል አራት ጠረጴዛዎች፤ መሥዋዕቱ የሚታረድባቸው በድምሩ ስምንት ጠረጴዛዎች አሉ ማለት ነው።
ከዚያም ያ ሰው በሰሜኑ በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አመጣኝ፤ እኔም ተመለከትሁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞልቶት አየሁ፤ በግንባሬም ተደፋሁ።