Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 40:38

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእያንዳንዱ የውስጥ መግቢያ በር መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚታጠብበት በር ያለው ክፍል አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የምድር ቤቱ መግቢያ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ ጐን ሲሆን፣ ወደ መካከለኛውና ከዚያም ወደ መጨረሻው ፎቅ የሚያስወጣ ደረጃ ነበረው።

ደግሞም መንፈስ ቅዱስ በልቡ ያሳደረውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አደባባይ፣ በዙሪያው ያሉትን ክፍሎች ሁሉ፣ የአምላክን ቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶችና የንዋየ ቅድሳቱን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ሰጠው፤

እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ ዐምስቱን በደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎቹ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ ገንዳው ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር።

ከዚህ በፊት የእህል ቍርባኑ፣ ዕጣኑ፣ የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች፣ የእህሉ ዐሥራትና፣ ለሌዋውያን፣ ለመዘምራንና ለበር ጠባቂዎች የታዘዘው አዲሱ ወይንና ዘይት፣ ለካህናቱም የሚመጣው ስጦታ ይቀመጥበት የነበረውን ትልቁን የዕቃ ቤት እንዲኖርበት ሰጥቶት ነበር።

ክፍሎቹንም እንዲያነጹ ትእዛዝ ሰጠሁ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች፣ የእህሉን ቍርባንና ዕጣኑን ጭምር መልሼ አስገባሁ።

ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤

ባሮክም በብራና ላይ የተጻፈውን የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ፤ “አዲሱ በር” በሚባለው በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ በሚገኘው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል ውስጥ ሆኖ ለሕዝቡ ሁሉ አነበበው።

በእያንዳንዱ ዘብ ቤት ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ የግንብ ዐጥር አለ፤ የዘብ ቤቶቹም ስፋት እኩል በኩል ስድስት ክንድ ነበር።

ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ እዚያም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ክፍሎችና ድንጋይ የተነጠፈበት መመላለሻ አየሁ፤ በመመላለሻውም ዙሪያ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።

በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ በደቡብ ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “በደቡብ ትይዩ ያለው ክፍል በቤተ መቅደስ ውስጥ ለሚያገለግሉ ካህናት ሲሆን፣

በሰሜን ትይዩ ያለው ክፍል ደግሞ በመሠዊያው ላይ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህም የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ማገልገል የሚችሉ ሌዋውያን እነርሱ ብቻ ናቸው።”

ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና።

አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑ መባውን ሁሉ አምጥቶ በመሠዊያው ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።

አቅራቢው የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መባውን ሁሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።

ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ አጠበ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ በጉን በሙሉ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።

ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች