Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 40:16

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ክፍሎቹ እንደ መተላለፊያ በረንዳዎቹ ከግራና ከቀኝ በኩል ትንንሽ መስኮቶች አሏቸው። በዙሪያው ያሉ መስኮቶች በመግቢያው በር ፊት ለፊት የነበሩ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ክፍል ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመቅደሱ ግድግዳ ዙሪያ ላይ ሁሉ በውስጥም በውጭም ኪሩቤልን፣ ከዘንባባ ዛፎችና ከፈነዱ አበቦች ጋራ ቀረጸ።

በሁለቱ የወይራ ዕንጨት መዝጊያዎችም ላይ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈነዱ አበቦችን ቀረጸ፤ በወርቅም ለበጣቸው።

ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችንም ቀረጸባቸው፤ ቅርጹን ሠራ፤ ጥሩ አድርጎም በወርቅ ለበጠው።

ለቤተ መቅደሱም ባለዐይነ ርግብ መስኮቶች አበጀ።

መስኮቶቹም ከፍ ብለው የተሠሩ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ።

የቤተ መቅደሱን ዋና ክፍል በጥድ ዕንጨት አልብሶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳልም ቀረጸበት።

ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ።

በእያንዳንዱ ዘብ ቤት ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ የግንብ ዐጥር አለ፤ የዘብ ቤቶቹም ስፋት እኩል በኩል ስድስት ክንድ ነበር።

ከበሩ መግቢያ እስከ መተላለፊያ በረንዳው መጨረሻ ድረስ ያለው ርቀት ዐምሳ ክንድ ነበር።

የመግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳው እንደ ሌሎቹ ሁሉ በዙሪያው ጠባብ መስኮቶች ነበሩት፤ ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፤ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

ከመተላለፊያ በረንዳው ትይዩ የሆኑ ሰባት ደረጃዎች ወደ መግቢያው በር ያመራሉ፤ ወጣ ወጣ ብለው በሚታዩ ግድግዳዎችም ላይ የዘንባባ ቅርጽ አለ።

የዘብ ቤቶቹ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳዎቹ ዙሪያቸውን መስኮቶች ነበሯቸው። ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

በውስጠኛው አደባባይ ዙሪያ ያሉት የመግቢያው በር መተላለፊያ በረንዳዎቹ ርዝመት ሃያ ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ወርዳቸው ደግሞ ዐምስት ክንድ ነበር።

መተላለፊያ በረንዳው ከውጭው አደባባይ ጋራ ትይዩ ነው፤ የዘንባባ ዛፎች በዐምዶቹ ላይ ተቀርጸዋል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

የዘብ ቤቶቹ፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር፤ መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳዎቹ ዙሪያቸውን መስኮቶች ነበሯቸው፤ ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

መተላለፊያ በረንዳው ከውጩ አደባባይ ትይዩ ነው፤ በዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

የዘብ ቤቶቹ፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦቹና መተላለፊያ በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር፤ በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩት። የዚህም ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

መተላለፊያ በረንዳው ከውጩ አደባባይ ትይዩ ነው፤ በዐምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል፤ እስከ መግቢያው ድረስም ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።

የዘብ ጠባቂ ቤቶች፣ ቁመታቸው አንድ መለኪያ ዘንግ፣ ወርዳቸውም አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር፤ በቤቶቹም መካከል ያሉት ግንቦች ውፍረት ዐምስት ክንድ ነበር። ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ባለው መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ መድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበር።

ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ተቀርጸውበት ነበር፤ የዘንባባ ዛፎቹ የተቀረጹት በኪሩብና በኪሩብ መካከል ነበር። እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው፤

በግንቦቹ ላይ እንዳለው ሁሉ በውስጡ መቅደስ በሮችም ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸዋል፤ በመተላለፊያ በረንዳውም ፊት ለፊት የዕንጨት መዝጊያ ተንጠልጥሏል።

በመተላለፊያ በረንዳውም ግራና ቀኝ ግንብ ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጽ ያለባቸው ጠባብ መስኮቶች ነበሩ። ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎችም በደረጃው በኩል የሚሸፍን ጣራ ነበራቸው።

ከዚያም ወደ ውስጥ ገባ፤ የመግቢያውን ዐምዶች ለካ፤ የእያንዳንዱም ወርድ ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ሲሆን፣ ግራና ቀኝ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር።

ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ።

በኢየሩሳሌም፣ በበጎች በር አጠገብ፣ ዐምስት ባለመጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጠመቂያ አለች።

አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያ ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያ ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች