በግራ እጅህ ያለውን ቀስትህን እመታለሁ፤ በቀኝ እጅህ የያዝሃቸውንም ፍላጾች አስረግፍሃለሁ።
“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።
በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ
አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም።
ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ እንዲሁም እጐትትሃለሁ፤ ከሩቅ ሰሜን አምጥቼ በእስራኤል ተራሮች ላይ እሰድድሃለሁ።
በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ፣ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።”
ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም።