ጋሻ የያዙና የራስ ቍር የደፉት ሁሉ፣ ፋርስ፣ ኢትዮጵያና ፉጥ ከእነርሱ ጋራ ይሆናሉ።
የካም ልጆች፦ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።
ኵሽ የናምሩድን አባት ነበረ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ።
የካም ወንዶች ልጆች፤ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን።
ከሰይፍ የተረፉትን ቅሬታዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እስከ ፋርስ መንግሥት መነሣትም ድረስ የእርሱና የልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ።
በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ ዓመት፣ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤
“ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥ አገለገሉ፤ ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።
በግብጽ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤ በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል። የታረዱት በግብጽ ሲወድቁ፣ ሀብቷ ይወሰዳል፤ መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።
ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ሉድም መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብጽ ጋራ በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።
ያየኸው ባለሁለት ቀንዶች አውራ በግ፣ የሜዶንና የፋርስን መንግሥታት ያመለክታል።
ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።