“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቀደመው ዘመን በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገርሁለት ያ ሰው አንተ አይደለህምን? በዚያ ወቅት አንተን በእነርሱ ላይ እንደማመጣባቸው ለብዙ ዓመታት ትንቢት ተናገሩ።”
በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።
ከሩቅ ያሉትን ሕዝቦች የሚጠራበትን ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻም በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነርሱም እየተጣደፉ በፍጥነት ይመጣሉ።
ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፤ በፊታቸው ቅድስናዬን ስገልጥ ሕዝቦች እኔን ያውቁ ዘንድ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
አሁን ግን ብዙ አሕዛብ፣ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል፤ እነርሱም፣ “የረከሰች ትሁን፤ ዐይናችንም ጽዮንን መዘባበቻ አድርጎ ይያት” ይላሉ።