ተራሮችህን በሬሳ እሞላለሁ፤ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ በተራሮችህ፣ በሸለቆዎችህና በውሃ መውረጃዎችህ ሁሉ ላይ ይወድቃሉ።
ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተዉት ሄደዋል።
እስከ ተራሮች ባለው መንገድ ሁሉ፣ በሚፈስሰው ደምህ ምድሪቱን አርሳታለሁ፤ ሸለቆዎችም በሥጋህ ይሞላሉ።
የሴይርን ተራራ ባድማና ጠፍ አደርጋለሁ፤ በርሱም ላይ የሚወጡትንና የሚወርዱትን አስቀራለሁ።