እርሱም በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ቢነፋ፣
እያንዳንዱም ግንበኛ ቅጥሩን በሚሠራበት ጊዜ ሰይፉን በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ መለከት የሚነፋው ሰው ግን ከእኔ አይለይም ነበር።
የመለከት ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ወደ እኛ ተሰብሰቡ። አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።”
“በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር።
“ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤ በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤ ‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ!’
“በምድር ሁሉ ላይ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ! በሕዝቦች መካከል መለከትን ንፉ! ሕዝቦችን ለጦርነት በርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትን፣ የሚኒንና የአስከናዝን መንግሥታት፣ ጠርታችሁ በርሷ ሰብስቧቸው፤ የጦር አዝማች ሹሙባት፤ ፈረሶችንም እንደ አንበጣ መንጋ ስደዱባት።
“እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።
ነገር ግን ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው፣ ከኀጢአቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እርሱ በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ነፍስህን ታድናለህ።
“መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ! ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ። በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ እርሱም በደጅ ነው።
የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?
ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፣ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?