“ፈርዖን ሆይ፤ አንተም እንደዚሁ ትሰበራለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት ከእነዚያ ካልተገረዙት ጋራ ትጋደማለህ።
ከዘመናት በፊት ከወደቁት ከኀያላን ሰዎች፣ ከእነዚያ ሰይፋቸውን ተንተርሰው፣ ጋሻቸውንም ደረታቸው ላይ ይዘው ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ መቃብር ከወረዱት ጋራ አይጋደሙምን? የእነዚህ ተዋጊዎች ሽብር በሕያዋን ምድር ባሉት ያልተገረዙ ኀያላን ላይ ቢደርስም፣ የኀጢአታቸው ቅጣት በዐጥንታቸው ላይ ይሆናል።
“ኤዶምም በዚያ አለች፤ ንጉሦቿና ገዦቿም ሁሉ በዚያ አሉ፤ ኀይል የነበራቸው ቢሆኑም፣ በሰይፍ ከተገደሉት ጋራ ተጋድመዋል፤ ወደ ጕድጓድ ከወረዱት ከእነዚያ ካልተገረዙትም ጋራ ተኝተዋል።