እነርሱም በሰይፍ ከተገደሉት መካከል ይወድቃሉ፤ ሰይፉ ተመዝዟል፤ ከብዙ ሰራዊቷ ሁሉ ጋራ ትጐተት።
በልባቸው ተንኰል እያለ፣ ከባልንጀሮቻቸው ጋራ በሰላም ከሚናገሩ፣ ከክፉ አድራጊዎችና ከዐመፃ ሰዎች ጋራ ጐትተህ አትውሰደኝ።
ወደ ሞት የሚነዱትን ታደጋቸው፤ እየተጐተቱ ለዕርድ የሚሄዱትን አድናቸው።
አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል፤ ከኢየሩሳሌም በሮች ውጪ፤ ተጐትቶ ይጣላል።
ከአሕዛብ መካከል ከርሱ ጋራ ያበሩ፣ በጥላው ሥር የኖሩ፣ በሰይፍ ከሞቱት ጋራ ለመቀላቀል ወደ መቃብር ወርደዋል።