ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋራ፣ ውበቱ ግሩም ነበር፤ ብዙ ውሃ ወዳለበት፣ ሥሮቹ ጠልቀው ነበርና።
የሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በቅርንጫፎቹ ላይ ጐጇቸውን ሠሩ፤ የምድር አራዊት ሁሉ፣ ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ። ታላላቅ መንግሥታትም ሁሉ፣ ከጥላው ሥር ኖሩ።
በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያሉ ዝግባዎች፣ ሊወዳደሩት አልቻሉም፤ የጥድ ዛፎች፣ የርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤ የኤርሞን ዛፎችም፣ ከርሱ ቅርንጫፎች ጋራ አይወዳደሩም፤ በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ በውበት አይደርስበትም።
ቅጠሎቹ ያማሩ፣ ፍሬዎቹ የተንዠረገጉ ነበሩ፤ በላዩም ለሁሉ የሚሆን ምግብ ነበረበት። የምድር አራዊት ከጥላው በታች ያርፉ ነበር፤ በቅርንጫፎቹም ላይ የሰማይ ወፎች ይኖሩ ነበር፤ ፍጥረትም ሁሉ ከርሱ ይመገብ ነበር።