Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 30:18

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል። በደመና ትሸፈናለች፤ መንደሮቿም ይማረካሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድሩ ሁሉ ጠቍሮ እስኪጨልም ድረስ አለበሱት። ከበረዶ የተረፈውን፣ በመስክ ላይ የበቀለውንና በዛፍ ላይ ያለውን ፍሬ ሁሉ ጠርገው በሉ። በግብጽ ምድር ሁሉ በዛፍ ላይ ወይም በተክል ላይ አንዳች ቅጠል አልተረፈም ነበር።

በዚያ ቀን ሸክማቸው ከትከሻህ፣ ቀንበራቸውም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል፤ ከውፍረትህም የተነሣ ቀንበሩ ይሰበራል።

የሰማይ ከዋክብትና ሰራዊታቸው፣ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።

ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ።

አሦርን በምድሬ ላይ አደቅቃለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”

ስለ ግብጽ የተነገረ ንግር፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤ የግብጻውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።

በዚያ ቀን እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኹበታል፤ ማንም ወደ ምድር ቢመለከት፣ ጨለማንና መከራን ያያል፤ ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጋረዳል።

በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

ደግሞም የሜምፊስና የጣፍናስ ሰዎች፣ መኻል ዐናትሽን ላጩሽ።

እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የዕንጨት ቀንበር ሠርተህ በጠፍር ማነቆ አያይዘውና በዐንገትህ አስገባው፤

ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ ዐንገት ወስዶ ሰበረው፤

“ሄደህ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አንተ የዕንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤ እኔ ግን በምትኩ የብረት ቀንበር እሠራለሁ።

“ ‘በዚያ ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤ እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዟቸውም።

በግብጽ ሰሜናዊ ክፍል በሚግዶል፣ በጣፍናስና በሜምፊስ እንዲሁም በግብጽ ደቡባዊ ክፍል ስለሚኖሩት የአይሁድ ሕዝብ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤

“ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’

ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።

ከመንግሥታት ሁሉ አነስተኛ ትሆናለች፤ ከሌሎችም አሕዛብ በላይ ራሷን ከፍ ማድረግ አትችልም። እጅግ ደካማ አደርጋታለሁ፤ ስለዚህ ሌሎችን አሕዛብ እንደ ገና መግዛት አትችልም።

ግብጻውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።

ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደመና ቀን፣ ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።

“ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

አንተን በማጠፋ ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሓይን በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።

የየሜዳው ዛፍ ፍሬ ይሰጣል፤ መሬቱም እህል ያበቅላል። ሕዝቡም በምድሪቱ ላይ ያለ ሥጋት ይኖራሉ። የቀንበሮቻቸውን ማነቆ ሰብሬ በባርነት ከገዟቸው እጅ ሳድናቸው፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ ያሉት ብዙ ሕዝቦች እንደ ማዕበል ትወጣላችሁ፤ ምድርን እንደሚሸፍን ደመናም ትሆናላችሁ።

ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ከእንግዲህ አያበሩም።

ለግብጻውያን ባሪያዎች እንዳትሆኑ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነት ቀንበራችሁን ሰብሬ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።

“ወዲያውኑ ከእነዚያ ከመከራው ቀናት በኋላ፣ “ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፤ ጨረቃ ብርሃኗን ትከለክላለች፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናጋሉ።’




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች