የግብጽ ምሽግ በሆነችው፣ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።
እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።
ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ በቴብስ ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
በግብጽ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤ ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤ ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።
ከዚያም ለሰባቱ መላእክት፣ “ሂዱ፤ ሰባቱን የእግዚአብሔር ቍጣ ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከቤተ መቅደሱ ሰማሁ።