ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለእግዚአብሔር ዐምድ ይቆማል።
እርሱም መጥቶ ግብጽን ይወጋል፤ ሞት የሚገባቸውን ለሞት፣ ለምርኮ የተመደቡትን ወደ ምርኮ፣ ለሰይፍ የተዳረጉትን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።
በጣፍናስም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
ስለ ሕዝቦች ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
በሃያ ሰባተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙር፤ በርሱና በግብጽ ሁሉ ላይ ትንቢት ተናገር፤
“በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም አፍህን እከፍታለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤ “ወዮ ለዚያ ቀን!”
በሕያዋን ምድር ሽብር እንዲያስፋፋ ብፈቅድም እንኳ፣ ፈርዖንና ሰራዊቱ ሁሉ በሰይፍ ከተገደሉት ጋራ ባልተገረዙት መካከል ይጋደማሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”