Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 29:7

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእጃቸው ሲይዙህ ተሰንጥረህ ትከሻቸውን ወጋህ፤ ሲደገፉህም ተሰብረህ ጀርባቸውን አጐበጥህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል፣ የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።

በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣ በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።

በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብጽ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።

ነገር ግን የፈርዖን ከለላ ውርደት ይሆንባችኋል፤ የግብጽም ጥላ ኀፍረት ያመጣባችኋል።

እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት! የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።

ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ ዐይኖቻችን ደከሙ፤ ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።

ግብጽ ከእንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ መታመኛ አትሆንም፤ ለርዳታ ወደ እርሷ ዘወር ባሉ ጊዜ ላደረጉት ኀጢአት ግን መታሰቢያ ትሆናለች። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ ተሰድዳም ሄደች። በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤ በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።

ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች