ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣ “አምላክ ነኝ” ትላለህን? በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
“ ‘እነሆ የእኅትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበር፤ እርሷና ሴት ልጆቿ እብሪተኞች፣ ጥጋበኞችና ደንታ ቢሶች ነበሩ፤ ድኾችንና ችግረኞችንም አይረዱም ነበር።
በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙትን ሰዎች አሟሟት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ ዙፋን ላይ፣ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ። ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፤ በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣ በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።
ያለ ሥጋት የኖረች፣ ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤ እርሷም በልቧ፣ “እኔ ብቻ ነኝ! ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።