Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 28:7

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣ በአንተ ላይ አመጣለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፤ ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤ ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።

በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ።

“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣ ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብጽን ሕዝብ እደመስሳለሁ።

ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣ ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤ ሰይፋቸውን በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤

ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተዉት ሄደዋል።

ከሕዝቦች ሁሉ እጅግ ጨካኝ በሆኑት፣ በኀያላን ሰዎች ሰይፍ፣ ያከማቸኸው ሰራዊት እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ የግብጽን ኵራት ያንኰታኵታሉ፤ የሰራዊቷም ብዛት ይጠፋል፤

እጅግ የከፉትን ከአሕዛብ አምጥቼ ቤቶቻቸውን እንዲነጥቁ አደርጋለሁ፣ የኀያላኑንም ትዕቢት አጠፋለሁ፤ መቅደሳቸውም ይረክሳል።

“ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኀይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፣ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።

የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች