ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
የጢሮስንና የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፣ ከባሕሩ ማዶ ያሉ የጠረፍ ምድር ነገሥታትን፣
በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።
በሌሎች ሕዝቦች መካከል ያሉ ነጋዴዎች ምንኛ አፏጩብሽ! መጨረሻሽ አስደንጋጭ ሆነ፤ ለዘላለምም አትገኚም።’ ”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለጢሮስ ገዥ እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ልብህ በትዕቢት ተወጥሮ፣ “እኔ አምላክ ነኝ፤ በአምላክ ዙፋን ላይ፣ በባሕሮችም ልብ ተቀምጫለሁ” አልህ። ምንም እንኳ እንደ አምላክ ጠቢብ ነኝ ብለህ ብታስብም፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
ደግሞም በአዋሳኟ በሐማት፣ ጥበበኞች ቢሆኑም እንኳ በጢሮስና በሲዶና ላይ ያርፍባቸዋል።
ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።