ዳርቻሽ በባሕር መካከል ነው፤ ሠሪዎችሽም ፍጹም ውብ አድርገውሻል።
እኔ ጌታ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፤ በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች፤ አሕዛብም ይበዘብዟታል፤
በባሕር መግቢያ ላይ ለምትገኘውና በብዙ ጠረፎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋራ ለምትነግደው ለጢሮስ እንዲህ በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጢሮስ ሆይ፤ “ፍጹም ውብ ነኝ” ብለሻል፤
ሳንቃዎችሽን ሁሉ፣ ከሳኔር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ ደቀልንም ይሠሩልሽ ዘንድ፤ ከሊባኖስ ዝግባ አመጡ።
ከተፈጠርህበት ቀን ጀምሮ፣ ክፋት እስከ ተገኘብህ ድረስ፣ በመንገድህ ነቀፋ አልነበረብህም።
በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ።