ቀዛፊዎች ሁሉ፣ መርከባቸውን ጥለው ይሄዳሉ፤ መርከብ ነጂዎችና መርከበኞችም ሁሉ፣ ወርደው ባሕሩ ዳር ይቆማሉ፤
የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’
ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።
ሕዝቦች በአንተ ላይ ከደረሰው የተነሣ እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌን በፊታቸው ስነቀንቅ፣ በአንተ ላይ ከደረሰው ሁኔታ የተነሣ ንጉሦቻቸው ይንቀጠቀጣሉ። አንተ በምትወድቅበት ቀን፣ እያንዳንዳቸው ስለ ራሳቸው ሕይወት በመፍራት፣ በየቅጽበቱ ይርበደበዳሉ።
በማታውቀው ምድር፣ በሕዝቦች መካከል ያንተን ጥፋት ሳመጣ፣ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።