የአራድና የሔሌክ ሰዎች፣ ቅጥርሽን በየአቅጣጫው ጠበቁ፤ የገማድ ሰዎችም፣ በምሽግሽ ውስጥ ነበሩ። ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።
ዐንገትሽ አምሮ የተሠራውን በላዩም የጦረኞች ጋሻዎች ሁሉ ያሉበትን፣ ሺሕ ጋሻዎች የተንጠለጠሉበትን፣ የዳዊትን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
“ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥ አገለገሉ፤ ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።
“ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።
ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።