Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 25:14

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሕዝቤ በእስራኤል አማካይነት ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እነርሱም እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ሕዝብ ላይ ያደርጋሉ፤ ኤዶማውያንም በቀሌን ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችም ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ተደፍተው እጅ ይንሡህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህ የተባረኩ ይሁኑ።”

በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።

ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣ የጦርነት ውካታ ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣ ከአገሯ ታስወጣለች፤” ይላል እግዚአብሔር፤

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እሟገትልሻለሁ፣ በቀልሽንም እኔ እበቀልልሻለሁ፤ ባሕሯን አደርቃለሁ፣ የምንጮቿንም ውሃ።

በታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በመዓቴም እቀጣቸዋለሁ፤” በምበቀላቸውም ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከጥላቻችሁ የተነሣ በእነርሱ ላይ በገለጣችሁት ቍጣና ቅናት ልክ እፈርድባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ፣ ማንነቴ በእነርሱ መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ።

የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ስዬ፣ እጄ ለፍርድ ስትይዘው፣ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ የሚጠሉኝንም እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።

አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ያነጻልና።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች