ድምፅህን ዝቅ አድርገህ በሐዘን አንጐራጕር እንጂ ለሞተው አታልቅስ። ጥምጥምህን ከራስህ አታውርድ፤ ጫማህንም አታውልቅ፤ አፍህ ድረስ አትሸፋፈን፤ የዕዝን እንጀራም አትብላ።”
ዳዊት ግን እያለቀሰ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፤ ራሱን ተከናንቦ፣ ባዶ እግሩን ነበር፤ ዐብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ሽቅብ ይወጣ ነበር።
በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።
ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።
“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።
ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣ “የክብር ዘውዳችሁ ከራሳችሁ ይወድቃልና፣ ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።
እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፤ ሚስቴም ማታውኑ ሞተች፤ በማግስቱም ጧት እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።
በራሳቸው ላይ ከበፍታ ፈትል የተሠራ ጥምጥም ያድርጉ፤ እንዲሁም ከበፍታ ፈትል የተሠራ ሱሪ በወገባቸው ላይ ይታጠቁ፤ እንዲያልባቸው የሚያደርግ ማንኛውንም ልብስ አይልበሱ።
የወይን ጠጅን ቍርባን ለእግዚአብሔር አያፈስሱም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሠኘውም፤ እንዲህ ዐይነቱ መሥዋዕት ለእነርሱ የሐዘንተኞች እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበሉትም ሁሉ ይረክሳሉ። ይህ ምግብ ለገዛ ራሳቸው ይሆናል፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ አይገባም።
ሙሴም አሮንንና የአሮንን ልጆች፣ አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “እንዳትሞቱ፣ በሕዝቡም ላይ ቍጣ እንዳይመጣ ጠጕራችሁን አትንጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በእሳት ስላጠፋቸው ሰዎች ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ሊያለቅሱላቸው ይችላሉ።
“እንዲህ ያለ ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጕሩን ይግለጥ፤ እስከ አፍንጫውም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ! ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ።
“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤ ወይም ልብሱን አይቅደድ።
ጌታ እግዚአብሔር፣ “በዚያ ቀን የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ወደ ዋይታ ይለወጣል፤ እጅግ ብዙ የሆነ የሰው ሬሳ ወድቆ ይገኛል፤ ዝምታም ይሰፍናል” ይላል።
ባለራእዮች ያፍራሉ፤ ጠንቋዮችም ይዋረዳሉ፤ ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፤ ከእግዚአብሔር መልስ የለምና።”
እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል።
ኢየሱስ ወደ ሹሙ ቤት እንደ ደረሰ እንቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ፣