ማገዶውን ከምርበት፤ እሳቱን አንድድ፤ ቅመም ጨምረህበት፣ ሥጋውን በሚገባ ቀቅል፤ ዐጥንቱም ይረር።
አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ሳለ ዔሳው እጅግ ተርቦ ከዱር መጣ።
በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣ በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣ መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ ለብዝበዛ አደርገዋለሁ።
የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ።
ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።”
ጕድፉ እንዲቀልጥ፣ ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣ መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው።
“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት! እኔም ደግሞ የምትቃጠልበትን ማገዶ እቈልላለሁ።