Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 23:32

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣ የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ ትጠግቢአለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላቸዋለሁ፤ ስለ ስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስም እተወዋለሁ፤ ከዚያም እስራኤል በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ይሆናሉ፤

ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤ ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።

ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ እንደ ውሃ አፈሰሱ፤ የሚቀብራቸውም አልተገኘም።

ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ!

የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤

“እግዚአብሔርን ንቋልና፣ ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ ለመዘባበቻም ይሁን።

ይህም ኀጢአትሽ ከመገለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን በዙሪያሽ ሆነው ለሚንቁሽ ለኤዶም ሴት ልጆችና ለጎረቤቶቿ ሁሉ፣ እንዲሁም ለፍልስጥኤም ሴት ልጆች መሣለቂያ ሆነሻል።

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ በልባችሁ ክፋት ሁሉ፣ በእስራኤል ውድቀት ላይ በመደሰት በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፤ በመዝለልም ጨፍራችኋልና

“የሰው ልጅ ሆይ! ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም፣ ‘ዕሠይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች፤ ደጆቿም ወለል ብለው ተከፈቱልኝ፤ እንግዲህ እርሷ ስለ ፈራረሰች እኔ እከብራለሁ’ ብላለችና፤

የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነች ጊዜ ስለ ተደሰትህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፤ አንተና መላዋ ኤዶም ባድማ ትሆናላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ።

“በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ መካከል፤ በአጠገብሽም በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሣለቂያ አደርግሻለሁ።

በቍጣና በመዓት፣ እንዲሁም በጭካኔ ፍርድ በማመጣብሽ ጊዜ፣ በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ ዘንድ የመሣቂያና የመሣለቂያ፣ የተግሣጽና የማስደንገጫ ምልክት ትሆኛለሽ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው፤ መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በዚህም ምክንያት በግብጽ ምድር፣ መዘባበቻ ይሆናሉ።”

ጠላቴ ሆይ፤ በእኔ ላይ በደረሰው ደስ አይበልሽ! ብወድቅም እንኳ እነሣለሁ፤ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔ ይሆናል።

እግዚአብሔር እንድትገባ በሚያደርግበት ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ፣ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናለህ።

ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት።

በሰጠችው መጠን ብድራቷን መልሱላት፤ ለሠራችው ሁሉ ዕጥፍ ክፈሏት፤ በቀላቀለችውም ጽዋ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች