Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 21:28

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰይፍ! ሰይፍ! ሊገድል የተመዘዘ፣ ሊያጠፋ የተጠረገ፣ እንደ መብረቅ ሊያብረቀርቅ የተወለወለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ የባቢሎናውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ፈጀ፤ ወጣቱንም ሆነ ወጣቲቱን፣ ሽማግሌውንም ሆነ በዕድሜ የገፋውን አላስቀረም፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠው።

“አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤ የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል። ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤ ጕልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።

በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣ አጥፊዎች ይሰማራሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣ አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤ የሚተርፍም የለም።

ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።

“ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’

ከንጉሣውያን ቤተ ሰብ አንዱን ወስዶ ከርሱ ጋራ ውል አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው፤ የምድሪቱንም ታላላቅ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤

ንጉሡ ግን በርሱ ላይ ዐመፀ፤ ፈረሶችና ብዙ ሰራዊት ለማግኘት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ይሳካለት ይሆን? እንዲህ ዐይነቱን ነገር የፈጸመ ያመልጣልን? ውል ያፈረሰስ ሳይቀጣ ይቀራልን?

በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ ለሚመጣው ሰይፍ አንደኛውን መንገድ ምልክት አድርግ፤ በይሁዳና በተመሸገችው ከተማ በኢየሩሳሌም ላይ ለሚመጣውም ሰይፍ ሁለተኛውን መንገድ ምልክት አድርግ።

ከእንግዲህ የሕዝቦችን ዘለፋ እንድትሰሙ አላደርግም፤ በሰዎችም ስድብ አትሠቃዩም፤ ከእንግዲህ ለሕዝባችሁ መሰናክል አትሆኑም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

በጊብዓ እንደ ነበረው፣ በርኩሰት ውስጥ ተዘፍቀዋል፤ እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፤ ስለ ኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች