Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 21:23

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም ከርሱ ጋራ ቃል ኪዳን ለገቡት የተሳሳተ የጥንቈላ ምሪት ይመስላል፤ እርሱ ግን በደላቸውን ያሳስባቸዋል፤ ማርኮም ይዟቸው ይሄዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሷም ኤልያስን፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ እኔ ምን አደረግሁህ? እዚህ የመጣኸው ኀጢአቴን አስታውሰህ ልጄን ለመግደል ነውን?” አለችው።

እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

እንደዚሁም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ዐንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ እንጂ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም።

እነርሱም፣ ‘ቤቶች የሚሠሩበት ጊዜ ቅርብ አይደለምን? ይህች ከተማ ድስት ናት፤ እኛም ሥጋ ነን’ ብለዋል።

“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር፣ ‘ዘመኑ ረዝሟል፤ ራእዩ ሁሉ ከንቱ ሆኗል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?

“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተ በምታደርጉት ሁሉ ኀጢአታችሁን በመግለጽ፣ በግልጽም በማመፅ በደላችሁን ስላሳሰባችሁ፣ እንዲህም ስላደረጋችሁ በምርኮ ትወሰዳላችሁ።

ግብጽ ከእንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ መታመኛ አትሆንም፤ ለርዳታ ወደ እርሷ ዘወር ባሉ ጊዜ ላደረጉት ኀጢአት ግን መታሰቢያ ትሆናለች። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

ወደ ካህኑ ይውሰዳት፤ ስለ እርሷም አንድ ኪሎ ገብስ ዱቄት ለቍርባን ይውሰድ፤ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አይጨምርበት፤ ይህ ስለ ቅናት የቀረበ የእህል ቍርባን በደልን የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና።

ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች