በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ ለሚመጣው ሰይፍ አንደኛውን መንገድ ምልክት አድርግ፤ በይሁዳና በተመሸገችው ከተማ በኢየሩሳሌም ላይ ለሚመጣውም ሰይፍ ሁለተኛውን መንገድ ምልክት አድርግ።
በዚያ ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያንን ከተማ ረባትን ወግቶ የቤተ መንግሥቱን ምሽግ ያዘ።
ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባት።
ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማእዘኑ በር፣ በሸለቆው በርና በቅጥሩ ማእዘን ማማዎች ሠርቶ መሸጋቸው።
ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ።
ከዚህ በኋላ በሸለቆው ውስጥ ከሚገኘው ከግዮን ምንጭ ምዕራብ አንሥቶ እስከ ዓሣ በር መግቢያ ድረስ ያለውን የዳዊትን ከተማ የውጭውን ቅጥር፣ የዖፌልን ኰረብታ እንዲከብብ በማድረግ፣ ይበልጥ ከፍ አድርጎ እንደ ገና ሠራው። በተመሸጉትም የይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጦር አዛዦችን አኖረ።
በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።
ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣ የጦርነት ውካታ ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣ ከአገሯ ታስወጣለች፤” ይላል እግዚአብሔር፤
ጠላቶችም ሆኑ ወራሪዎች፣ የኢየሩሳሌምን በሮች ጥሰው ይገባሉ ብለው፣ የምድር ነገሥታት፣ ወይም ከዓለም ሕዝብ አንዳቸውም አላመኑም።
የረባት ከተማ የግመሎች መሰማሪያ፣ አሞንንም የበጎች መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣ በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣ ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።
ከራፋይማውያን ወገን የተረፈ የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ ነበር። ዐልጋው ከብረት የተሠራ ቁመቱም ዘጠኝ ክንድ፣ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። ይህም እስካሁን በአሞናውያን ከተማ በረባት ይገኛል።