ነገር ግን ከግብጽ ሳወጣቸው ባዩ አሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ እጄን ሰበሰብሁ።
እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤ በግርማህም አታስፈራራኝ፤
ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣ ለስምህ ክብርን ስጥ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።
እርሱ ግን መሓሪ እንደ መሆኑ፣ በደላቸውን ይቅር አለ፤ አላጠፋቸውም፤ ቍጣውን ብዙ ጊዜ ገታ፤ መዓቱንም ሁሉ አላወረደም።
ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፤ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ። ከእኛ ጋራ የገባኸውን ኪዳን ዐስብ፤ አታፍርሰውም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።
በጽዮን ሴት ልጅ ዙሪያ ያለውን ቅጥር፣ እግዚአብሔር ለማፍረስ ወሰነ፤ የመለኪያ ገመድ ዘረጋ፤ ከማጥፋትም እጆቹን አልሰበሰበም፤ ምሽጎችና ቅጥሮች እንዲያለቅሱ አደረገ፤ በአንድነትም ጠፉ።
ነገር ግን ከመካከላቸው ሳወጣቸው ባዩ አሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስለ ስሜ ተቈጠብሁ።
እኔ ግን በርኅራኄ ተመለከትኋቸው እንጂ አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም አልፈጀኋቸውም።
ነገር ግን በመካከላቸው በኖሩባቸውና እስራኤልን ከግብጽ ምድር ለመታደግ ቃል ስገባ፣ በእነርሱ ዘንድ በተገለጥሁት በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስለ ስሜ ክብር ተቈጠብሁ።
“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደ ፈረሰው መቅደስ መልስ።
ጌታ ሆይ፤ ስማ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ተመልከት እና ርምጃ ውሰድ! ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና፣ አምላኬ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።”