በዙሪያው ያሉ አሕዛብ ተነሡበት፤ ከየአገሩም ሁሉ ተሰበሰቡበት፤ መረባቸውን ዘረጉበት፤ በጕድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ።
የጦር አለቆቹ ከበባ በሚያደርጉበትም ሰዓት ንጉሥ ናቡከደነፆር ራሱ ወደ ከተማዪቱ መጣ።
አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል፤ ከኢየሩሳሌም በሮች ውጪ፤ ተጐትቶ ይጣላል።
በእግዚአብሔር የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ በወጥመዳቸው ተያዘ፤ በጥላው ሥር፣ በአሕዛብ መካከል እንኖራለን ብለን አስበን ነበር።
መረቤን በርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ነገር ግን እርሷን ሳያያት በዚያ ይሞታል።
መረቤን በላዩ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል። ወደ ባቢሎን እወስደዋለሁ፤ በእኔ ላይ ስላመፀም በዚያ እፈርድበታለሁ።
አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤ በጕድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤ እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።
ምሽጎቻቸውን አወደመ፤ ከተሞቻቸውንም ባድማ አደረገ፤ ምድሪቷና በውስጧ ያሉት ሁሉ፣ ከግሣቱ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።