ሰውን ባይጨቍን፣ ብድር ለመስጠት መያዣ ባይጠይቅ፣ በጕልበቱ ባይቀማ፣ ነገር ግን ምግቡን ለተራበ፣ ልብሱን ለተራቈተ ቢሰጥ፣
ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ ሰዎችን ገፍፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።
የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤ የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።
“ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣
በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣
በበጎቼ ጠጕር ስላሞቅሁት፣ ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣
ብፁዕ ነው፤ ለድኾች የሚያስብ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።
ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ ምግቡን ከድኾች ጋራ ይካፈላልና።
ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም ውሃ አጠጣው።
ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።
ድኻውንና ችግረኛውን ቢጨቍን፣ በጕልበት ቢቀማ፣ በመያዣነት የወሰደውን ባይመልስ፣ ወደ ጣዖታት ቢመለከት፣ አስጸያፊ ተግባራትን ቢፈጽም፣
“በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ባይበላ፣ በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት ባይመለከት፣ የባልንጀራውን ሚስት ባያባልግ፣
ማንንም አይጨቍንም፤ ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣ በጕልበት አይቀማም።
ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል፤
ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ አስታምማችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’
ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም ንጹሕ ይሆንላችኋል።
ነገር ግን ግብዣ ባዘጋጀህ ጊዜ ድኾችን፣ አካለ ስንኩሎችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውሮችን ጥራ፤