“ነገር ግን ይህ ሰው ደም የሚያፈስ ወይም ከሚከተሉት ኀጢአቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፣
“ሰውን ደብድቦ የገደለ ሞት ይገባዋል።
“አንድ ሌባ በር ሲሰብር ተይዞ ቢደበደብና ቢሞት፣ ተከላካዩ የደም ባለዕዳ አይሆንም፤
አባትየው አንዱንም ባያደርግ፣ “ልጁ ግን በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ቢበላ፣ የባልንጀራውን ሚስት ቢያባልግ፣
ሥርዐቴን ይከተላል፤ ሕጌንም በቅንነት ይጠብቃል። ይህ ሰው ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።
“ ‘ባልንጀራህን አታጭበርብር፤ አትቀማውም። “ ‘የሙያተኛውን ደመወዝ ሳትከፍል አታሳድር።
“ ‘ነፍስ ያጠፋን፣ በመግደል ወንጀል ተጠያቂ የሆነን ሰው ጉማ አትቀበሉ፤ ፈጽሞ መሞት አለበት።
እነርሱም እንደ ገና በመጮኽ፣ “የለም፤ እርሱን አይደለም! በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።
የክፉው ወገን ሆኖ ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ፤ ለምን ገደለው? ምክንያቱም የርሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።