በታበይሽበት ወቅት የእኅትሽን የሰዶምን ስም ለመጥራት እንኳ ፈቃደኛ አልነበርሽም፤
‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
እኅቶችሽ ሰዶምና ሴት ልጆቿ እንዲሁም ሰማርያና ሴት ልጆቿ ቀድሞ ወደ ነበሩበት ሁኔታ ይመለሳሉ፤ አንቺና ሴት ልጆችሽም ቀድሞ ወደ ነበራችሁበት ሁኔታ ትመለሳላችሁ።
ይህም ኀጢአትሽ ከመገለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን በዙሪያሽ ሆነው ለሚንቁሽ ለኤዶም ሴት ልጆችና ለጎረቤቶቿ ሁሉ፣ እንዲሁም ለፍልስጥኤም ሴት ልጆች መሣለቂያ ሆነሻል።
በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ፣ በዚያ ቀን አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን፣ ከዚህች ከተማ አስወግዳለሁና፤ ከእንግዲህ ወዲያ፣ በቅዱስ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም።
ፈሪሳዊውም ቆሞ ስለ ራሱ እንዲህ ይጸልይ ነበር፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ይልቁንም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለመሆኔ አመሰግንሃለሁ፤