ኵራተኞች ነበሩ፤ በፊቴ አስጸያፊ ተግባር መፈጸማቸውን ባየሁ ጊዜም አስወገድኋቸው።
የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጥኣን ነበሩ።
ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት እጅግ በዝቷል፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከፍቷል፤
ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው።
እነዚያንም ከተሞችና ረባዳውን ምድር በሙሉ፣ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፣ የምድሩን ቡቃያ ሳይቀር ገለባበጠው።
ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት።
እንዲሁም ስለ አምልኮ ባዕድ ሥርዐት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የቤተ ጣዖት ወንደቃዎችን ክፍሎችና ሴቶች ለአሼራ መጋረጃ የሚፈትሉባቸውን ክፍሎች አፈረሰ።
ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።
ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።
ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።
የመንግሥታት ዕንቍ፣ የከለዳውያን ትምክሕት የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።
ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣ እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤ በማለዳ ዋይታን፣ በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤
በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋራ፣ ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።
እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣ በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀረኋቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።
በሕዝቤ ላይ የደረሰው ቅጣት፣ የማንም እጅ ሳይረዳት፣ በድንገት ከተገለበጠችው፣ ሰዶም ላይ ከደረሰው ቅጣት ይልቅ ታላቅ ነው።
“ ‘ከሴት ጋራ እንደሚደረገው ሁሉ ከወንድ ጋራ አትተኛ፤ ይህ አስጸያፊ ነው።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”
ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን።
ምድሪቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች። አንዳች ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አያቈጠቍጥባትም፤ የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የሚደርስባት ውድመት እግዚአብሔር በታላቅ ቍጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፣ እንደ አዳማና ስቦይ ጥፋት ይሆናል።
ደግሞም ኀጢአት ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ እንዲሆኑ፣ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ፣ በዙሪያቸውም ያሉ ከተሞች ለሴሰኛነትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት በመቀጣት ለሚሠቃዩት ምሳሌ ሆነዋል።
“ከርሷ ጋራ ያመነዘሩና በምቾት የኖሩ የምድር ነገሥታት፣ እርሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ ስለ እርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝናሉም።