በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ።
ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ ኀፍረትሽ ይታይ፤ እበቀላለሁ፤ እኔ ማንንም ሰው አልተውም።”
“ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ ራስሽን ብትጠይቂ፣ ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣ በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።
“ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤
“ሊባኖስ ላይ ወጥተሽ ጩኺ፤ ድምፅሽን በባሳን አሰሚ፤ በዓባሪም ሆነሽ ጩኺ፤ ወዳጆችሽ ሁሉ ወድመዋልና።
አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፤ ምን መሆንሽ ነው? ቀይ ቀሚስ የለበስሽው ለምንድን ነው? ለምን በወርቅ አጌጥሽ? ዐይኖችሽንስ ለምን ተኳልሽ? እንዲያው በከንቱ ተሽሞንሙነሻል፤ የተወዳጀሻቸው ንቀውሻልና፤ ነፍስሽንም ሊያጠፉ ይፈልጋሉ።
“ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነርሱ ግን ከዱኝ፤ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ፣ ምግብ ሲፈልጉ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ዐለቁ።
ኢየሩሳሌም ከባድ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህም የረከሰች ሆናለች፤ ያከበሯት ሁሉ ናቋት፤ ዕራቍቷን ሆና አይተዋታልና፤ እርሷ ራሷ ታጕረመርማለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር ብላለች።
ይህም ኀጢአትሽ ከመገለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን በዙሪያሽ ሆነው ለሚንቁሽ ለኤዶም ሴት ልጆችና ለጎረቤቶቿ ሁሉ፣ እንዲሁም ለፍልስጥኤም ሴት ልጆች መሣለቂያ ሆነሻል።
ባቢሎናውያንም መጥተው ወደ ፍቅር መኝታዋ ገቡ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት፤ እርሷም በእነርሱ ከረከሰች በኋላ ጠልታቸው ከእነርሱ ዘወር አለች።
አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ ነውሯን እገልጣለሁ፤ ከእጄም የሚያድናት የለም።
አለዚያ ገፍፌ ዕርቃኗን አስቀራታለሁ፤ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፤ እንደ ምድረ በዳ፣ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።
በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣ እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ በንጉሥና በአለቆች ጭቈና ሥር፣ እየመነመኑ ይሄዳሉ።
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች አመንዝራዪቱን ይጠሏታል፤ ባዶዋንና ዕራቍቷን ያስቀሯታል። ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።