ማንኛዋም አመንዝራ ሴት ዋጋ ይከፈላታል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ስጦታ ታበረክቻለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋራ ያመነዝሩ ዘንድ እጅ መንሻ ታቀርቢላቸዋለሽ።
ነገር ግን የፈርዖን ከለላ ውርደት ይሆንባችኋል፤ የግብጽም ጥላ ኀፍረት ያመጣባችኋል።
የወይራ ዘይት ይዘሽ፣ ሽቱ በላዩ ጨምረሽ ወደ ሞሎክ ሄድሽ፤ መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ አገር ላክሽ፤ እስከ ራሱ እስከ ሲኦልም ዘለቅሽ!
በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።
“ ‘አንቺ ከገዛ ባሏ ይልቅ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ነሽ!
ስለዚህ ያንቺ ግልሙትና ከሌሎቹ የተለየ ነው፤ ማመንዘር የሚሻ ማንም ሰው፣ አንቺን አሳድዶ ማግባባት አያስፈልገውም። ዋጋ ትከፍያለሽ እንጂ አይከፈልሽም፤ አንቺ የሌሎች ፍጹም ተቃራኒ ነሽ።
ቤቶችሽን ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶችም ፊት ቅጣት ያመጡብሻል። ግልሙትናሽን አስተውሻለሁ፤ ከእንግዲህም ለወዳጆችሽ ዋጋ አትከፍዪም።
ከውሽሞቼ የተቀበልሁት ዋጋ ነው የምትለውን የወይን ተክሎቿንና የበለስ ዛፎቿን አጠፋለሁ፤ ጫካ አደርገዋለሁ፤ የዱር አራዊትም ይበሉታል።
በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ወንዶች ልጆችን በዝሙት ዐዳሪዎች ለወጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም፣ ሴቶች ልጆችን ሸጡ።
ጣዖቶቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤ ምስሎቿን ሁሉ እደመስሳለሁ፤ ገጸ በረከቷን በዝሙት ዐዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣ አሁንም ገጸ በረከቷ የዝሙት ዐዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።”
ነገር ግን ይህ ልጅህ ንብረትህን ከጋለሞቶች ጋራ አውድሞ ሲመጣ፣ የሠባውን ፍሪዳ ዐረድህለት።’