Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 16:16

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከልብስሽ አንዳንዱን ወስደሽ የምታመነዝሪበትን መስገጃ ስፍራ አስጌጥሽበት፤ እንዲህ ዐይነት ነገር ከዚህ ቀደም አልታየም፤ ወደ ፊትም አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ስለ አምልኮ ባዕድ ሥርዐት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የቤተ ጣዖት ወንደቃዎችን ክፍሎችና ሴቶች ለአሼራ መጋረጃ የሚፈትሉባቸውን ክፍሎች አፈረሰ።

አካዝ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ ወሰደ፤ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሮች ዘጋ፤ በኢየሩሳሌምም በየአውራ ጐዳናው ማእዘን ላይ መሠዊያ አቆመ።

ዐልጋሽን ከፍ ባለውና በረጅሙ ኰረብታ ላይ አነጠፍሽ፤ በዚያም መሥዋዕትሽን ልታቀርቢ ወጣሽ።

“ወደ ኪቲም ጠረፍ ተሻገሩና እዩ፤ ወደ ቄዳርም ልካችሁ በጥንቃቄ መርምሩ፣ እንዲህ ዐይነት ነገር ተደርጎ ያውቅ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤

“ ‘ነገር ግን በውበትሽ ተመካሽ፤ ዝናሽንም ለአመንዝራነት ተጠቀምሽበት፤ ከዐላፊ አግዳሚው ጋራ ያለ ገደብ አመነዘርሽ፣ ውበትሽም ለማንም ሆነ።

ከሰጠሁሽ ወርቄና ብሬ የተሠራውን ምርጥ ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አበጀሽ፤ ከእነርሱም ጋራ ዝሙት ፈጸምሽ።

ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

በውብ ዕንቋቸው ታብየዋል፤ ይህንም አስጸያፊ የጣዖት ምስሎቻቸውንና ርኩስ ቅርጻ ቅርጾችን ለመሥራት ተጠቅመውበታል። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ወደ ርኩሰት እለውጥባቸዋለሁ።

አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ ነውሯን እገልጣለሁ፤ ከእጄም የሚያድናት የለም።

እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣ እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች