ሰው ይኖርባቸው የነበሩ ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”
ከተማዪቱ ፈጽማ ፈርሳለች፤ በሮቿም ደቅቀው ወድቀዋል።
ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ ጨርሶም ትበዘበዛለች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሯልና።
የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘እነሆ፤ በዐይናችሁ ፊት፣ በዘመናችሁም የደስታና የሐሤት ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስወግዳለሁ።’
እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ።
የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤
እነሆ፤ አዝዛቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደዚህችም ከተማ እንደ ገና እመልሳቸዋለሁ። እነርሱም ይወጓታል፤ ይይዟታል፤ በእሳትም ያቃጥሏታል። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው፣ ባድማ አደርጋቸዋለሁ።’ ”
አንበሳ ከደኑ ወጥቷል፤ ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቷል፤ ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ ከስፍራው ወጥቷል። ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።
ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣ የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።
“በአሕዛብ መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከዱር ዛፎች መካከል የወይን ግንድ እንዲነድድ ለእሳት አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች አሳልፌ እሰጣለሁ።
ታማኝነትን ከማጕደላቸው የተነሣ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ።
“በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ መካከል፤ በአጠገብሽም በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሣለቂያ አደርግሻለሁ።
“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደ ፈረሰው መቅደስ መልስ።
ከተሞቻችሁን አፈራርሳለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም ወና አደርጋለሁ፤ ጣፋጭ ሽታ ያለውን መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም።
በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ።