ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ እልክባችኋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣ የናስ ቀስት ይወጋዋል።
የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።
ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”
በዚያም ለመኖር ወደ ግብጽ ለመሄድ የወሰኑ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር በርግጥ ይሞታሉ፤ ከማመጣባቸውም ጥፋት አንድ እንኳ የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይገኝም።’
እንዲሁ ብንተወው ሰው ሁሉ በርሱ ያምናል፤ ሮማውያንም መጥተው ስፍራችንንና ሕዝባችንን ይወስዱብናል።”