እግዚአብሔር በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “ከኪሩቤል ዘንድ ከመንኰራኵሮቹ መካከል እሳት ውሰድ” ብሎ ባዘዘው ጊዜ፣ ሰውየው ወደ ውስጥ ገብቶ በአንዱ መንኰራኵር አጠገብ ቆመ።
ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤ በብርሃንህ ተገለጥ።
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ።
እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “በኪሩቤል ሥር ወዳሉት መንኰራኵሮች መካከል ግባ፤ በኪሩቤል መካከል ካለውም የእሳት ፍም እጅህን ሞልተህ ዝገን፤ በከተማዪቱም ላይ በትነው” አለው። ሰውየውም እያየሁት ገባ።
ሁሉን ቻይ አምላክ ሲናገር እንደሚሰማው ድምፅ ዐይነት፣ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጪው አደባባይ ድረስ ይሰማ ነበር።
ከኪሩቤልም አንዱ በመካከላቸው ወዳለው እሳት እጁን ዘርግቶ ጥቂት ወሰደ፤ በፍታ በለበሰው ሰው እጅ ላይ አኖረው፤ እርሱም ይዞ ወጣ።
“እኔም ስመለከት፣ “ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፤ የራሱም ጠጕር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፤ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኰራኵሮቹም ሁሉ እንደሚነድድ እሳት ነበሩ።