Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ሕዝቅኤል 1:18

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የመንኰራኵሮቹ ክብ ጠርዝ ረዥምና አስፈሪ ነበር፤ የአራቱም መንኰራኵሮች ክብ ጠርዝ ዙሪያውን በዐይኖች የተሞላ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንኰራኵሮቹ የሠረገላ መንኰራኵር መሰል ሲሆኑ፣ ወስከምቶቹ የመንኰራኵሮቹ ክፈፎችና ዐቃፊዎቻቸው እንዲሁም ወስከምቶቹ የሚገቡባቸው ቧንቧዎች በሙሉ ከቀለጠ ብረት የተሠሩ ነበሩ።

የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።

“ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

ጀርባቸውን፣ እጃቸውን፣ ክንፋቸውን ጨምሮ መላ ሰውነታቸው እንዲሁም አራቱ መንኰራኵሮቻቸው በጠቅላላ በዐይን የተሞሉ ነበሩ።

“የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱ በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”

ደግሞም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት የጠራ የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑ መካከል፣ በዙሪያውም ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።

አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች ነበሯቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸው በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ፤ ቀንና ሌሊትም፦ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ” ማለትን አያቋርጡም።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች